መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ሽያጩን ለማፋጠን የአክሲዮን ሻጭ ኤጀንት ሊጠቀም መሆኑ ተገለጸ
የቦርዱ ም/ሰብሳቢ እና የማርኬቲንግ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተስፋየ ቢሆነኝ ዛሬ ጥቅምት 9 2013 ዓ.ም እንደተናገሩት ያቀድናቸውን እቅዶች በቶሎ ወደ ሥራ ለማስገባት የአክዮን ሻጭ ኤጀንት መጠቀሙ አስፈላጊ መሆኑን ተናገሩ፡፡ የአክሲዮን ማኅበሩ የማርኬቲንግ ቡድን ከሚሠራው ሥራ በተጨማሪ የአክሲዮን ሻጭ ኤጀንት መጠቀሙ የበለጠ ውጤታማ ሊያደርገን ስለሚችል ከአክሲዮን ሻጭ ኤጀንት ጋር መዋዋሉ አስፈላጊ መሆኑን ቦርዱ ስላመነበት ከዚህ በፊት ልምድ ያላቸውን በማወዳደር አንድ የአክሲዮን ሻጭ ኤጀንት መመረጡን እና ከተመረጠውም ድርጅት ጋር ውል ለመግባት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡