የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በአክሲዮን ሽያጭ ዙሪያ የሚነሱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ምላሽ

በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻ ገበያ ሥርዓት ተጠቅመው በጤናው ዘርፍ ላይ በማተኮር በገቢና ወጭ ንግድ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሁሉ የተሻለ አማራጭ በመሆንና አገልግሎት በማቅረብ ለሀገሪቱ አጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት
የሚጠበቅባቸውን ተገቢ ድርሻ ለማበርከት አስበውና ራዕይ ሰንቀው በተነሱ በጤናው ዘርፍ እና በሌሎች የሙያ ዘርፎች የካበተ ልምድ ባላቸው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ አክሲዮን ማኅበር ነው

የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ሁሉንም መስፈርቶች አሟልቶ በኢትዮጵያ በንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የተመዘገበ ሕጋዊ ተቋም ሲሆን

  • በምዝገባ ቁጥር ፡ AR/AA/3/0006864/2013
  • በምዝገባ ቀን፡ 12/01/2013 ዓ.ም. ተመዝግቧል

መሥራቾቹ 102 ሲሆኑ ከ 85 የሚበልጡት በጤናው ዘርፍ ሰፊ የሥራ ልምድ ከበቂ በላይ የሙያ ስብጥርና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው እንዲሁም በአስተዳደር፣ ፋይናንስ እና ተቋማትን በመምራት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ከ 15 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸው

  • ቦርድ አባላቱ ዘጠኝ ሲሆኑ በሙያ ስብጥራቸው፣ በልምዳቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ
    የደረሱ፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው፣ ታማኞች እና ለቆሙለት ዓላማ ቆርጠው
    የሚሠሩ ናቸው
  • ስላላቸው የሥራ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት ለማወቅ በድረ ገጻችን
    www.meqrezhealth.com/board ላይ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

በፍጥነት ከገዙ አዎ በትክክል ይችላሉ!!!

መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. በታኅሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው አንደኛ አስቸኳይ ስብሰባ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ፈጥነው እስከ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አክሲዮን ለሚገዙ ባለአክሲዮኖች መሥራች እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡ ስለዚህ መሥራች አባል መሆን ይቻላል፡፡

በትክክል!

መሥራች የሆኑ ባለአክሲዮኖች አክሲዮን ማኅበሩ ማትረፍ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ከተጣራው ትርፍ 10 በመቶውን ባላቸው አክሲዮን መጠን ይከፋፈላሉ፡፡ ቀሪውን 90 በመቶውን ደግሞ ከሌሎች ጋር በመሆን ባላቸው አክሲዮን መጠን ይከፋፈላሉ፡፡

  • እያደገ ያለውን የታካሚዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የህክምና አገልግሎት ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላትና በመስጠት፣ በግሉ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ሀገራችንን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማዳን፤
  • በሀገራችን ተወዳዳሪ የሆነ፣ የታካሚዎችን ፍላጎት በማርካት ላይ ያተኮረ ተመራጭ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መሆንና ከሀገራችን ውጭ ለሚገኙ ዜጎች ተመራጭ የህክምና ማዕከል በመሆን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ለሀገሪችን ኢኮኖሚ የበኩሉን ድርሻ ለመውጣ፤
  • ለኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥነትን
    በመቀነስ ድርሻን ለመወጣት፤
  • የባለአክሲዮኖችና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማሟላት፤
  • በውጭ ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደ ሀገራቸው መጥተው እንዲያገለግሉ ተገቢውን ለማድረግ፤
  • ደረጃቸውን ከጠበቁ ዓለም ዐቀፍ የህክምና ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት

በጤናው ዘርፍ

  • ጠቅላላ ሆስፒታሎች፤
  • ዲያግኖስቲክ ማዕከላት፤
  • መድኃኒትና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች አስመጭና አከፋፋይ ንግድ ሥራ ላይ ለመሰማራት፤
  • ተርሸሪ ሆስፒታል ለማቋቋምና ሚዲካል ሲቲ ለመመስረት፤
  •  የማማከርና ምርምር አገልግሎት ለመስጠት፤

በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ

በትምህርት ዘርፍ ይሰማራል

ከዚህም ውስጥ በመጀመሪያ ዙር ከሚተገበሩ ተግባራት ውስጥ:

  • ጠቅላላ ሆስፒታል
  • ኢሜጂንግ ዲያግኖስቲክ ማዕከል
  • መድኃኒትና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች አስመጭና አከፋፋይ
  • ፋርማሲዎች
  • የማማከርና የምርምር አገልግሎት ናቸው

የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ የተፈቀደ ካፒታል ብር 1 ቢሊየን ሲሆን በመጀመሪያ ደረጃ ለሚሠራቸው ሥራዎች የሚያስፈልገው የብር መጠን ብር 522,170,000.00 ብር ነው፡፡

በዓላማው ማመን፤እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነው ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ማንነትን የሚገልጽና የታደሰ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፓስፖርት በማቅረብ አክሲዮን ለመግዛት ይችላል

  • ኢትዮጵየውያን
  • ትውልደ ኢትዮጵያውያን
  • የኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ ወኪሎች
  • ግለሰብ በተናጠል እና በጣምራ
  • የንግድ ድርጅቶች
  • የሃይማኖት ተቋማት
  • ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች
  • የእርዳታ ድርጅቶች
  • ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ
  • የጸና ፓሰፖርት ኮፒ
  • የሚገዙትን የአክሲዮን መጠን ባሉበት ሀገር ሆነው በተከፈቱት የባንክ ሒሳቦች በሀገራችን ተቀባይነት ባላቸው የሐዋላ መንገዶች ገቢ ማድረግ ወይም ከውጪ ምንዛሬ ሒሳባቸው ላይ በመክፈል
  • የተዘጋጀውን ቅጽ በድረ ገጹ ላይ በኦን ላይን ወይም ከድረ ገጽ በማውረድ መሙላትና በኢሜል መላክ ወይም በተወካይ በኩል ቅጹን በመሙላት በቀላሉ መግዛት ይችላሉ

አክሲዮኑን ለመግዛት የግድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሚለው ካርድ አስፈላጊ ነው
ቢሆንም ለማሳደስ የሚወስደው ጊዜ ስላለ መሥራች የመሆኑን እድል እንዳያጡት
በማሰብ አክሲዮኑን አሁን ገዝተው እና ቅጹን ሞልተው ቢጫ ካርድዎን በፍጥነት
አሳድሰው እንደላኩልን የድርጅቱን ደረሰኝ ቆርጠን የምንልክልዎ መሆኑን ሆኖም ግን
በተባለው የአክሲዮን ሽያጭ ወቅት(እስከ ሐምሌ 1 2013 ዓ.ም) አሳድሰው
የማይልኩልን ከሆነ ምዝገባውን የምንሰርዘው እና ገንዘብዎን ድርጅቱ ሥራ ከጀመረ
በኋላ የምንመልስልዎ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን

  • የአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 1000
  • ዝቅተኛው የግዢ መጠን ብር 20,000 ብር ሲሆን ከፍተኛው መጠን ብር 6,000,000
  • ለትውልደ ኢትዮጵያውያንም ዝቅተኛው የግዢ መጠን ተመሳሳይ ሆኖ በተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሬ መከፈል ይኖርበታል
  • የአክሲዮን ክፍያ በአንድ ጊዜ ወይም በሁለት ጊዜ ሊከፍሉ ይችላሉ
  • በአንድ ጊዜ ሙሉውን መክፈል አልያም ደግሞ በመጀመሪያ 50 በመቶውን ከፍለው ቀሪውን 50 በመቶውን ደግሞ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ መክፈል ያሻል

በሚገዙት የአክሲዮን መጠን አምስት በመቶ (5% ) ይኸም የአገልግሎት ክፍያ ከመጀመሪያው ክፍያ ጋር በተፈረመው ልክ ተሰልቶ በአንድ ጊዜ ብቻ ይከፈላል

በትክክል!

ለልጆችዎ አክሲዮኑን በመግዛት የወደፊት ሕልማቸውን ማሳካት ይችላሉ፡፡ ለልጆችዎ ለመግዛት ሲቀርቡ የልደት ምስክር ወረቀት ኮፒ፤ የእርስዎ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ ኮፒ እና ባንክ ያስገቡበትን ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የአሳዳጊውን ስም አስቀድሞ ለሕጻን እገሌ/እገሊት ብሎ የአክሲዮን መግዣ ቅጹ ላይ በመሙላት በስማቸው ሊገዙላቸው ይችላሉ

ይቻላል!

  • የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብና የእያንዳንዳቸውን መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፖስፖርት ኮፒ በማያያዝ እና የሚገዙትን የአክሲዮን መጠን በባንክ በማስገባት መግዛት ይቻላሉ
  • ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ዘመድ፣ ወዳጅና ሽሪክ ሁሉም መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፖስፖርት ኮፒ በማያያዝ እና የሚገዙትን የአክሲዮን መጠን በባንክ በማስገባት መግዛትይችላሉ
  • በኢትዮጵያ 10 ባንኮች የባንክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን ባንኮቹም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አቢሲንያ፣ አዋሽ፣ ሕብረት፣ቡና፣ ንብ፣ወጋገን፣ አባይ፣ ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ና ዳሸን ባንኮች ናቸው
  • የአክሲዮን ሽያጩ ከላይ በተዘረዘሩት ባንክ ቅርንጫፎች በሙሉ እና በመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. የአክሲዮን ሽያጩ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፣
  • ሀገር ውስጥ ውክልና ያለው ሰው ካለ ወይም ካሉበት ሆነው አስፈላጊውን መረጃ በድረ ገጹ ላይ ባለው ቅጽ በመሙላት መግዛት ይቻላል
  • ከኢትዮጵያ ውጪ በመካከለኛው ምሥራቅ፣በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ነዋሪ ሆነው ከሚያስተባብሩ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ገንዘቡን ከላይ በተዘረዘሩ ባንኮች በተመዘገቡ ሕጋዊ የሐዋላ መንገዶች በመላክ ወይም በባንኮች በተከፈቱት የውጪ ምንዛሬ ሒሳቦች ገንዘቡን በመላክ መግዛት ይቻላል
  • አክሲዮኑን ሲገዙ ከፈለጉ ባሉበት ሀገር ገንዘብ በቀጥታ መግዛት ወይም በኢትዮጵያ
    ብር ልከው መግዛት ይችላሉ
  • ያስገቡት የገንዘብ መጠን የሚሰላው በእለቱ ባለው ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው
    የኢትዮጵያ ብር የግዢ ምንዛሬ ይሆናል
  • ከ 1000 ብር በታች የሆነ ትርፍ የሚመጣ ካለ ተጨማሪ የጎደለውን በመሙላት
    አንድ አክሲዮን ማድረግ ይችላሉ
  • ማንነትዎን ከሚገልጽ ከታደሰ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፓስፖርት ጋር ባንክ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በመያዝ መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ የፕሮጀክት ጽ/ቤት መምጣትና በምትኩ የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ ደረሰኞች መውሰድ ይኖርብዎታል፤
  • ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆኑ ሲመችዎት ጽ/ቤት በመምጣት ወይም ለዘመድ ወዳጅ በመላክ ወይም ስካን አድርገው በድርጅቱ ኢሜይል በመላክ ወይም በአክሲዮን ማኅበሩ ድረ ገጽ አስፈላጊው ሰነድ በማስገባት የኦላይን ምዝገባ በመፈጸም እና የባንኩን ደረሰኝ በመላክ የአክሲዮን ማኅበሩን ደረሰኞችን መውሰድ ይኖርቦታል።
  • በትክክል! ይችላሉ
  • አክሲዮን ማኅበራችን ሁሉንም ሰው ባሉበት ቦታ ለመድረስ ካሉበት ሆነው አክሲዮኑን በኦላይን
    የሚገዙበትን ሁኔታ አመቻችቷል
  • በኦላይን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
    1. የታደሰ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፓስፖርት
    2. ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ የትውልደ ኢትዮጵያዊ ካርድ (yellow card)
    3. ተወካይ ከሆኑ የተሰጠዎትን ሕጋዊ ውክልና
    4. ገንዘቡን ባንክ ያስገቡበት ደረሰኝ
    5. ፊርማ
  • ከ 1-5 ያሉትን አስፈላጊ ሰነዶች ስካን በማድረግ ወይም ፎቶ በማንሳት ያዘጋጁ
  • ከዚያም በድረ ገጻችን www.meqrezhealth.com ላይ ለ ግለሰብ ወይም ለትውልደ ኢትዮጵያዊ ወይም ለድርጅት ከሚለው የሚፈልጉትን በመምረጥ መሙላት ይቻላል
  • በተጨማሪም ከላይ ከ 1-5 ያሉትም መረጃዎች ካደራጁ በኋላ በ ድረገጻችን ላይ በ Pdf
    ፎርማት የተቀመጠውን የአክሲዮን መግዣ ቅጽ በማውረድ በእጃችን ከሞላንና ከፈረምን በኋላ
    ከላይ ካዘጋጀናቸው መረጃዎች ጋር ስካን በማድረግ በ shares@meqrezhealth.com
    መላክ ይችላሉ
  • እነዚህን መረጃዎች በላኩ 48 ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ
    ባስመዘገቡት ኢሜይል እንልክሎታለን
  • በትክክል!
  • አክሲዮኑን እርስዎ በሚመችዎ ወቅት እና ጊዜ ወደ ራስዎ ስም እንዲዛወርልዎ የገዛልዎት ሰው
    ዋና ቢሯችን መጥቶ ለቦርዱ በማቅረብ ማዞር ይቻላል፤ በእርስዎ መሞላት የሚያስፈልገውን
    ሰነዶች በድረ ገጻችን ላይ ባለው የኦላይን መመዝገቢያ ወይም በእጅ ሞልተው መላክ ይችላሉ
  • በመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በኩል የሚጠየቁት ምንም አይነት ክፍያ
    አይኖረውም ፤ በመንግሥት በኩል ግን አክሲዮን ለማዛወር ክፍያ ሊኖረው ይችላል
  • በትክክል!
  • እርስዎ ይህንን ማኅበር ሲቀላቀሉ ዓላማውን ተረድተውት እንደሆነ ሁሉ የሚሸጡለትም ሰው
    በአክሲዮን ማኅበሩ ዓላማ የሚያምን፣ በመመሥረቻ ጽሑፉ፣ መተዳደሪያ ደንቡ እንዲሁም
    በተለያዩ ወቅቶች በጠቅላላ ጉባኤው ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዢ ለመሆን ዝግጁ የሆነ መሆን
    ይኖርበታል
  • መቅረዝ የተቋቋመ ድርጅት ስለሆነ ከታቀዱት አምስት ፕሮጀክቶች ውስጥ በመጀመሪያ
    የዲያግኖስቲክ ማእከሉን የሚያስጀምር ገንዘብ እንደተሰበሰበ ሥራውን ጀምሮ ጎን ለጎን
    ሌሎቹን ሥራዎችንም በፍጥነት ለመጀመር አክሲዮኖች እየሸጠ ይቀጥላል
  • ይኸም ገንዘባችን ብዙ ጊዜ ያለ ሥራ ባንክ ላይ እንዳይቀመጥ እና የተሻለ ትርፍን
    ለባለአክሲዮኖች እንዲያመጣ ያስችላል
  • ስለዚህ አክሲዮኑን በቶሎ በመግዛት ወደ ሥራ እንድንገባ የድርሻዎትን ይወጡ
  • ባደረግነው የአዋጭነት ጥናት በሀገራችን ውስጥ እየተካሄዱ ካሉ የቢዝነስ ዘርፎች የጤናው ዘርፍ
    በጣም አዋጪ እና ዝቅተኛ የመክሰር አደጋ ያለው መሆኑን ያሳያል
  • በዚህም መሠረት መቅረዝ የጤና አገልግሎት ባደረገው የአምስት አመት የአዋጭነት ጥናት
    በመጀመሪያው ዓመት 13 በመቶ በሁለተኛው ዓመት 26 በመቶ በሦስተኛው ዓመት 42 በመቶ
    በአራተኛው ዓመት 61 በመቶ እና በአምስተኛው ዓመት 90 በመቶ ትርፍ እንደሚያመጣ
    ያመላክታል
  • የወጣበትንም የኢንቨስትመንት ወጪ ከ ሁለት አመት ባነሰ ጊዜ እንደሚመልስ ያሳያል
  • በመሆኑን ከሌሎች ዘርፎች በተሻለ ትርፋማና አዋጪ ተቋም መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር
    ይቻላል
  • አዎ! የትርፍ ክፍፍሉ በየዓመቱ ባለዎት የአክሲዮን መጠን ልክ ሆኖ መጋቢት 30 2013 ዓ.ም
    አክሲዮን ከገዙ ደግሞ በተጨማሪ የመሥራችነት ጥቅም 10 በመቶ በገዙት የአክሲዮን መጠን
    ልክ ለተከታታይ ሦስት አመታት ይደርስዎታል
  • በአክሲዮን ማኅበሩ የወጣ የአክሲዮን ሽያጭ ካለ የትርፍ ክፍፍል ድርሻዎን አክሲዮን ማኅበሩ
    ላይ አክሲዮኖችን ለማሳደግ ሊያውሉት ይችላሉ
  • አክሲዮን ማኅበሩን ከተቀላቀሉ በኋላ ለያንዳንዱ ባለአክሲዮን በግሉ በሚከፈትለት መለያ ስም
    እና የይለፍ ቁጥር ወይንም በቴሌግራም በቀላሉ በመግባት የገዙትን የአክሲዮን መጠን፣
    የቀረብዎት የአክሲዮን ክፍያ ካለ፣ በትርፍ ክፍፍሉ የደረሰዎትን ድርሻ፣ አዲስ ተጨማሪ የወጡ
    አክሲዮኖች ብዛት፣ በአክሲዮን ማኅበሩ የሚላኩ መልእክቶችን በድረ ገጻችን ላይ ለባለአክሲዮን
    በሚለው ክፍል ( እየተዘጋጀ ያለ) ላይ በመግባት መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ

ይፍጠኑ!

  • የመሥራች አባል የመሆን እድል መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይጠናቀቃል
  • ሙሉ በሙሉ የአክሲዮን ሽያጩ ለ ዘጠኝ ወራት የሚቆይ ሲሆን በ ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ይጠናቀቃል

ዋና ጽ/ቤት በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-17ለ

  • ስልክ ቁጥር +251-991-737373
  • ኢሜል: MeQrezHS2020@gmail.com,info@meqrezhealth.com, shares@meqrezhealth.com
  • ድረ ገጽ፡ www.meqrezhealth.com
  • ቴሌግራም:@MeQrezHealth
  • facebook: fb.me/meqrezhealth

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ፍቅር እና አክብሮት የተሞላበት የላቀ እንክብካቤ

©2020. መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. ( ምዝገባ ቁጥር ፡ AR/AA/3/0006864/2013 የተመዘገበበት ቀን ፡ 12/01/2013 ዓ.ም.)
Website by eTech