የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ጥር 30 2013 ዓ.ም ብቻ አራዘመ
እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ በ ታኅሳስ 28 2013 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ጥር 30 2013 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ገለጸ፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ማኅተመ በቀለ ሲናገሩ ‘’በመጀመሪያም እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ’’ ካሉ በኋላ ቦርዱ የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ጥር 30 2013 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ተናግረው ያራዘመበትን ምክንያት ሲገልጡ ‘’ሀገራችን በጦርነት እና በፈተና ውስጥ ነበረች ይኸ ደግሞ ኅብረተሰቡ ላይ የሥነ አዕምሮ እና የኢኮኖሚ ጫና አሳድሮ ስለነበር ወቅቱ ለሁላችንም በጣም ፈታኝ ነበር፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ እየተሻገርነው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ብዙ ሰዎችን ለመድረስ እንዲረዳ እና ብዙዎችም እንዲራዘም ስለጠየቁ ጊዜውን ለአንድ ወር ብቻ እስከ ጥር 30 ማራዘም አስፈላጊ ሆኗል፡፡’’
እስካሁን ስላለው የአክሲዮን ሽያጭ ሒደትም ሲናገሩ ‘’ምንም እንኳን እንደ ሀገር ያሳለፍነው ጊዜ ከባድ ቢሆንም እስካሁን ያለው የአክሲዮን ሽያጭ በጣም ጥሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡’’ በመጨረሻም ሲያጠቃልሉ ‘’የተራዘመው ለአንድ ወር ጊዜ ብቻ ስለሆነ ጊዜው ሳይጠናቀቅ በፍጥነት አክሲዮኑን በመግዛት ሁላችሁም መሥራች ባለ አክሲዮን እንድትሆኑ ለማስታወስ እወዳለው’’ ብለዋል፡፡