መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ

መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር እሁድ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ለሆስፒታል አገልግሎት በተከራየው ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞው ግራንደ ዮርዳኖስ ሆቴል አካሄዷል፡፡ በጉባኤውም ላይ ሼር ከገዙ ባለአክሲዮኖች 42 በመቶው በራሳቸው እና በተወካያቸው ተገኝተዋል፡፡ በጉባኤውም ላይ በአጠቃላይ ከ400 የሚበልጡ ባለአክሲዮኖች ተገኛተዋል፡፡ በጉባኤውም ላይ የሚከተሉት አጀንዳዎች ከጸደቁ በኋላ በምልዓተ ጉባኤው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1. የ2ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
2. አዳዲስ ባለ አክሲዮኖችን መቀበል፣
3. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2014 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መስማትና ማጽደቅ፣
4. የውጪ ኦዲተር ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ፣
5. በተጓደሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምትክ ተተኪ የቦርድ አባልትን ስለማጽደቅ፣
6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አክሲዮናቸውን ያሳደጉ ነባር፣ አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖችን በመወከል በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ቀርበው እንዲፈርሙ ውክልና ስለመስጠት፣
7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አበልን ማጽደቅ፣
8. አዲስ የሚገቡ ባለአክሲዮኖችን በመሥራች አባልነት እንዲመዘገቡ የሚቀበልበትን ጊዜ መወሰን
9. የ2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ናቸው፡፡

ከላይ በተቀመጡት አጀንዳዎች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ከተካሄደ በኋላ ቦርዱ ያቀረባቸውን የውሳኔ ሃሳቦች ላይ መጠነኛ ማስተካከያ በማድረግ በሙሉ ድምጽ ያለምንም ተቃውሞ በማጽደቅ ጠቅላላ ጉባኤው ከቀኑ 11፡05 ተጠናቋል፡፡