የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. (የአክሲዮን ሽያጭ መግለጫ)
1. መግቢያ
በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻ ገበያ ሥርዓት ተጠቅመው በጤናው ዘርፍ በማተኮር በገቢና ወጭ ንግድ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሁሉ የተሻለ አማራጭ በመሆንና አገልግሎት በማቅረብ ለሀገሪቱ አጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ተገቢ ድርሻ ለማበርከት አስበውና ራዕይ ሰንቀው ከዚህ በታች ስማቸው የተጠቀሱት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የቀድሞው አደራጆች በወጠኑት አላማ መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. ሊከውናቸው ካሰባቸው ተግባራት ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ቢተገበሩ ያላቸው የጠቅላላ ሆስፒታል፣የኢሜጂንግ ዲያግኖስቲክ ማዕከል፣ የመድኃኒት እና የሕክምና እቃዎች አስመጪና አከፋፋይ ፣ ፋርማሲ እንዲሁም የማማከር አገልግሎት ለመፈጸም የካፒታል ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አምነንበታል፡፡ በቀጣይ ደግሞ የቴርሺያሪ ሆስፒታል ግንባታን ጎን ለጎን መሥራት፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እና በትምህርት ዘርፍ የመሰማራት እቅድ አለው፡፡ ቦርዱ ይህንንም ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በታላቅ ታማኝነት ፣ቁርጠኝነት እና ሥነ ምግባር በተላበሰ መልኩ ለመከወን ዝግጁ ነው፡፡
ስለሆነም ቦርዱ በማያወላዳ ሁኔታና በማናቸውም ጊዜ የመልካም አስተዳደር የአሠራር ሥርዓት መኖሩን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ የ1952 ዓ.ም የንግድ ሕግ በተለይ የአክሲዮን ማኀበር አሠራር እና የካፒታል ማሳደግ ሒደትን በሚመለከት የተቀመጡትን ድንጋጌዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናት የሚያወጧቸውን ደንቦችና መመሪያዎች ሳይጣሱ በጥብቅ መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ግዴታ ገብተዋል፡፡ ዘላቂነቱ በሂደት ከተረጋገጠ እንዲሁም ከንቁና ታታሪ የማኔጅሜንት ቡድን ጋር፣ ከሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲሁም ዘመኑ ካፈራው ተፎካካሪ ቴክኖሎጂ ጋር በተቀናጀ የጤና ተቋማቱ ወደፊት በዓለም ደረጃ ስኬታማ ከሚባሉት መሰል ተቋማት ተርታ ሊሰለፉ እንደሚችል ይታመንበታል፡፡
2. አጭር የኘሮጀክቱ እቅድ መግለጫ
የመሥራች ባለአክሲዮኖች ብዛት | 102 |
የተከፈለ የአክሲዮን ብዛት | 4,170 |
የእያንዳንዱ አክሲዮን የነጠላ ዋጋ በብር | 1,000.00 |
የተከፈለ ጠቅላላ የአክሲዮን መጠን | 4,170,000.00 |
ለመጀመሪያ ደረጃ ሥራዎች በተጨማሪ የሚያስፈልግ የአክሲዮን ብዛት | 518,000 |
ለመጀመሪያ ደረጃ ሥራዎች በተጨማሪ የሚያስፈልግ የአክሲዮን መጠን በብር | 518,000,000.00 |
ድርጅቱን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስፈልግ የካፒታል መጠን በብር | 250,000,000.00 |
የአገልግሎት ክፍያ በእያንዳንዱ አክሲዮን በመቶ | 5%
|
መግዛት የሚፈቀደው ዝቅተኛ የአክሲዮን መጠን (ቁጥር) | 20 |
መግዛት የሚፈቀደው ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን (ቁጥር) | 6,000 |
የክፍያ ሁኔታ | – 50% በምዝገባ፣ 50% በ6 ወራት
– የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ጊዜ በሙሉ ይከፈላል |
የተፈረመ ካፒታል ያልተከፈለው መጠን ተከፍሎ መጠናቀቅ ያለበት ጊዜ | 6 ወራት |
አክሲዮኖች ተሽጠው የሚጠናቀቁበት ጊዜ | 9 ወራት |
ከወጭ ቀሪ የአገልግሎት ክፍያ | ለድርጅቱ ካፒታል ማሳደጊያ እንዲውል ይደረጋል |
የዋና መሥራቾች አደራጅ ኮሚቴ አባላት ጥቅም | አደራጆች የተቋማቱ ዕውን መሆን የሚሰጣቸውን እርካታን በማስቀደም ምንም ዓይነት ከትርፍ በመቶኛ ክፍያ አይኖራቸውም |
የመሥራች ባለአክሲዮኖች ጥቅም | የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ትርፍ የዓመታዊ ትርፍ 10% ለመሥራች ባለአክሲዮኖች (መሥራች አደራጆችን ጨምሮ) |
ለአማካሪዎች | ምሥጋናና የምሥክር ወረቀት በሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይሰጣል፡፡ |
ድርጅቱ ሥራ የሚጀምረው ደረጃውን በጠበቀ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ በኢሜጂንግ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ፣ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ ዕቃዎች አስመጭና አከፋፋይ ፣ ፋርማሲ እና የማማከር አገልግሎት ሆኖ የካፒታሉ መጠን (259,117,100.00፣ 154,814,000.00.00፣ 99,396,000.00 እና 8,842,900.00 በቅደም ተከተል) ድምር 522,170,000.00 ፣ ዝቅተኛው ሥራ የሚጀምርበት ካፒታል ብር 250,000,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሣ ሚሊዮን ብር) ሆኖ ይህም ገንዘብ ለሕዝብ ለሽያጭ በሚቀርቡ ተራ አክሲዮኖች የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡ እንደአስፈላጊነቱና አቅም በፈቀደ መጠን በጠቅላላ ጉባዔ ጸድቆ የተፈቀደው ካፒታል ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያድግ እየተደረገ መጀመሪያ እስከ ብር ሁለት ቢሊዮን በሂደት ደግሞ ከዚያም በላይ ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡
3. ዓላማ
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር ወደ ጤና አገልግሎት ዘርፍ ሲሰማራ ዋና ዓላማ ያደረጋቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ/ እያደገ ያለውን የታካሚዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የህክምና አገልግሎት ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላትና በመስጠት፣ በግሉ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ሀገራችንን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማዳን፤
ለ/ በሀገራችን ተወዳዳሪ የሆነ፣ የታካሚዎችን ፍላጎት በማርካት ላይ ያተኮረ ተመራጭ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መሆንና ከሀገራችን ውጭ ለሚገኙ ዜጎች ተመራጭ የህክምና ማዕከል በመሆን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ለሀገሪችን ኢኮኖሚ የበኩሉን ድርሻ ለመውጣ፤
ሐ/ ለኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥነትን በመቀነስ ድርሻን ለመወጣት፤
መ/ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማቋቋም፤
ሠ/ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ለማቋቋም፤
ረ/ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች አስመጭና አከፋፋይ ንግድ ሥራ ላይ ለመሰማራት፤
ሰ/ ተርሸሪ ሆስፒታል ለማቋቋምና ሚዲካል ሲቲ ለመመስረት፤
ሸ/ የማማከርና ምርምር አገልግሎት ለመስጠት፤
ቀ/ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሠማራት፤
በ/ በትምህርት ዘርፍ መሠማራት፤
ተ/ የባለአክሲዮኖችና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማሟላት፤
ቸ/ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደሀገራቸው መጥተው እንዲያገለግሉ ተገቢውን ለማድረግ፤
አ/ ደረጃቸውን ከጠበቁ ዓለም ዐቀፍ የህክምና ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት እና የመሳሰሉት ዓላማዎች አሉት፡፡
4. የመቅረዝ አ.ማ. ሕጋዊ ዋና መሥሪያ ቤት እና የቅርንጫፎች ቢሮዎች
አዲስ አበባ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና በዓለም ደረጃ 3ኛዋ ግዙፍ የዲኘሎማቲክ ማዕከል ናት፡፡ በተጨማሪ ልዩ ልዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መንግሥታዊ ኤጀንሲዎች ሕጋዊ/ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በየዕለቱ የኦኘሬሽን ሥራ ስለሚያገናኘን እንዲሁም አብዛኛው የሀገሪቱ የንግድ ማኅበረሰብን ያካተተ የቴክኖሎጂ መረጃ የመለዋወጥ አገልግሎቶች ስለሚሰጡበት የዋናው መሥሪያ ቤታችን ሕጋዊ መቀመጫ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 210/ 1-17ለ ነው፡፡
በቀጣይም በክልል ከተሞች እንዲሁም መለስተኛ ከተሞች በመሄድ ቅርንጫፍ እንዲከፈትበት የውሣኔ ሃሳብ በቀረበበት ሥፍራ የሕዝብ ብዛት የሚያሳይ ጥናት (የሕዝብ ቁጥር፣ የጾታ ስብጥር፣ዕድሜ) ፣በገጠሩ በቂ የጤና አገልግሎት የሌለበት አካባቢ በመሄድ ተደራሽ የመሆን ተግባራትም ይከወናሉ፡፡
5. የመቅረዝ አ.ማ. ርዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴት
ርዕይ
ለጥራት የሚተጋ በተገልጋዮች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው እና እጅግ ተመራጭ የሆነ የጤና እንክብካቤ ሰጪ መሆን
ተልዕኮ
በፍቅር የሚንከባከቡ ባለሙያዎችንና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጅዎች በመጠቀም በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጤና አገልግሎት መስጠት
ዕሴቶቻችን
የድርጅት ስኬት የሚመሠረተው ፈሪሃ እግዚአብሔር ባለው፣ በሰለጠነ፣ በሥነ- ምግባር በሚመራ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ ግኝቶች ጣምራ እንቅስቃሴ ውህደት ነው፡፡
ስለሆነም ቦርዱ፣ ማኔጅመንቱና የድርጅቱ ሠራተኛ ተጠያቂነትን የተላበሰ ሆኖ በጤናው ዘርፍና በአጠቃላይ ደግሞ ለሰፊው ሕዝብ አድናቆት የሚቸረው እሴት ማበርከት ሲሆን ለዚሁም ተቋሙ ከፍተኛውን የሞራልና የሥነ-ምግባር ደረጃ እንዲኖረው ማድረግና የሚከተሉትን ዕሴቶች በዋነኝነት ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፣
ዕሴቶች
- ፈሪሃ እግዚአብሔር
- ርኅራኄ
- ሌሎችን በፍቅር ማገልገል
- ርትዕ እና ሚዛናዊነት
- አክብሮት
- በጥምረት እና በትብብር መሥራት
- የቡድን ሥራ
- በዕውቀት እና በጥበብ መመራት
- ታማኝነት
- ተጠያቂነት
6. ዳይሬክተሮች
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሆነው የተመረጡት ይኸንን ተቋም ለማቋቋም ሀሳብ አፍላቂና አደራጆች በሆኑት ባለራዕዮች ነው፡፡ ምርጫው የተከናወነባቸው የምዘና መስፈርቶች ኘሮፊሽናልነት (የሙያ ብቃት) ፣ የትምህርት ደረጃ ክሂሎት፣ የሞራልና የሥነ-ምግባር ዕሴቶች እንዲሁም የድርጅቱ የወደፊት ኘሮጀክት የሚጠይቀውን ተክለ ሰውነት/ስብዕና እና ተገቢ የሥራ ልምድ ናቸው፡፡
በአሁኑ ወቅት ስማቸው፣አድራሻቸውና ልምዳቸው ከዚህ በታች ከ1-9 የተጠቀሰው ዳይሬክተሮች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በሂደት በሙሉ አባልነት ወይም በጊዜያዊነት በቡድን መልክ የሚዋቀሩ ሌሎች ተጨማሪ የፕሮጀክት ማናጀር፣የሒሳብ ባለሙያ፣ የሽያጭ ባለሙያዎች እንደአስፈላጊነቱ ይቀጠራሉ፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስም፣አድራሻ፣ የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ
ተ.ቁ. | የዳይሬክተሮች ስም | ጾታ | ዜግነት | የጋብቻ ሁኔታ | አድራሻ | የትምህርት ዝግጅት | የቀድሞና ያሁን የሥራ ልምድ/ኃላፊነት |
1 | ማኅተመ በቀለ ሙለታ (ዶ/ር) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ፡ አራዳ፣ ወረዳ ፡7፣ የቤት ቁ. ፡492፣ የ መ/ ሳጥን ቁጥር –1271
ስልክ ቁ. +251 (0)923794505፣አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና እስፔሻሊሲት እና የንቅለ-ተከላ ሰብ-እስፔሻሊሲት | ከ16 ዓመት በላይ በጤናው ዘርፍ በማስተማር፣ በማከም እና በመምራት ልምድ ያካበቱ |
2 | ናትናኤል ታዬ ጀንበሬ (ዶ/ር) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ፡ቦሌ ፣ ወረዳ: 09፣ የቤትቁጥር: አዲስ፣
ስልክ: +251911727263አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
የውስጥ ደዌ ሕክምና ስፔሻሊሲትእናየልብ ሕክምናሰብስፔሻሊሲት | ከ14 ዓመት በላይ በጤናው ዘርፍ በማስተማር፣ በማከም እና በመምራት ልምድ ያካበቱ |
3 | ታደሰ አሰፋ ጥሩነህ (አቶ) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ፡ቦሌ ፣ ወረዳ: 10፣ የቤትቁጥር: አዲስ፣
የ መ/ ሳጥን ቁጥር ፡2315 code1110፣ ስልክ: +251929918494 አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
ኤም. ቢኤ፣ ቢኤ ዲግሪ በማኔጅመንት፣ቢቲኤች | ከ20 ዓመት በላይ በሥራ አመራር ኃላፊነት ልምድ በሀገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች፣ የሥራ አመራር አማካሪ |
4 | ተስፋዬ ቢሆነኝ ትኩ (አቶ) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ: ቦሌ፣ ወረዳ: 15፣ የቤትቁጥር: አዲስ፣
ስልክ: +251913855556፣ አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
ኤም. ኤ በማርኬቲንግ ማናጅመንት ቢኤ ዲግሪ ቢዝነስ ማኔጅመንት | ከ 18 ዓመት በላይ በማስተማር እና በሥራ አመራር ኃላፊነት ልምድ |
5 | አንዱዓለም ኃይሉ ጉደታ (አቶ) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ፡ ኮ/ቀራንዮ ፣ወረዳ፡ 6፣ የቤት ቁጥር፡ 561 ፣ስልክ
+251911431444፣ አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
ኤም. ኤ በኢኮኖሚክ ፖሊሲ አስተዳደር፣ ቢኤ ዲግሪ በኢኮኖሚክስ | ከ18 ዓመታት በላይ በሥራ አመራር ኃላፊነት፣ስልታዊ እቅድ፣በባንክ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ የካበተ ልምድ |
6 | ሙሉዓለም ካሣ ስዩም (አቶ) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ፡ ን/ስ/ላፍቶ ፣ወረዳ ፡2፣ የቤት ቁጥር፡ ቢ35/03
ስልክ፡ +251930004080፣ አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
ኤም.ኤስ. ሲ በፋርማሱቲካል አናሊስስ እና ጥራት ማረጋገጥ፣ቢ.ኤስ. ሲ በኬሚስትሪ፣ | ከ 17 ዓመታት በላይ በሙያ እና በሥራ አመራር ኃላፊነት ልምድ |
7 | አምባቸው ተፈራ ምንዳ (ዶ/ር) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ፡ ቦሌ፣ ወረዳ፡ 2 ፣የቤት ቁጥር፡ 373፣
ስልክ፡+251911146889፣ አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
ኤም.ፒ. ኤች በኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ፣ ሜዲካል ዶክተር | ከ17 ዓመታት በላይ በጤናው ዘርፍ ፐሮጀክቶችን በመምራት እና በማማከር ልምድ ያላቸው |
8 | ዳዊት አለነ ደስታ (አቶ) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ፡ አዲስ ከተማ፣ ወረዳ፡ 7፣ የቤት ቁጥር፡ 297 ፣ስልክ፡+251911514728፣ አ.አ ፣ ኢትዮጵያ | ኤም.ኤስ. ሲ በጂኦቴክኒካል ኢንጂነሪንግ፣ ቢ.ኤስ. ሲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ | ከ 20 ዓመታት በላይ በኢንጂነሪንግ ሙያ እና በሥራ አመራር ኃላፊነት ልምድ |
9 | ሳሙኤል አያልነህ እጅጉ (ቀሲስ) | ወ | ኢትዮጵያዊ | ያገባ | ክፍለ ከተማ: ጉለሌ፣
ወረዳ: 04፣ የቤትቁጥር: 1026፣ ስልክ: +251912872622፣ አ.አ ፣ ኢትዮጵያ |
ኤም.ፒ. ኤች በኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ፣ ሜዲካል ላቦራቶሪ ቴክኖሎጂስት | ከ 13 ዓመታት በላይ በጤናው ዘርፍ በመምራት እና በማማከር ልምድ ያካበቱ |
7. የድርጀቱ መነሻ ካፒታል የአክሲዮኖች ብዛት እና ዋጋ
- የተፈቀዱ፣የተፈረሙና የተከፈሉ መነሻ አክሲዮኖች 4,170
- ድርጅቱን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስፈልግ ካፒታል፡
- በ2013 የሚሸጡ አክሲዮኖች 518,000
- የተከፈሉ አክሲዮኖች 4,170
- የእያንዳንዱ አክሲዮን የነጠላ ዋጋ ብር 1,000.00
- ድርጅቱን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስፈልገው የአክስዮን ብዛት 250,000
8. የአክሲዮኖች ክፍያ አፈጻጸም ሥርዓት
- የቅድሚያ (የመጀመሪያ እርከን) ክፍያ 50% ባለአክሲዮኖቹ ለመክፈል በተስማሙትና በፊርማቸው ባጸደቁት አክሲዮን የመግዛት ግዴታ መሠረትና በተጨማሪ ለሥራ ማስኬጃና ለሌሎች ወጪዎች የሚሆን በተፈረመው ላይ ኘሪሚየም ተሰልቶ የሚከፈል፡፡
- የሁለተኛውና የመጨረሻውን እርከን ክፍያ የአክሲዮን ግዢ ሽያጩን ለመፈጸም የውል ግዴታ ከተገባበት ቀን ጀምሮ በ6 (ስድስት) ወራት ውስጥ 50% ይከፈላል፡፡
- ባለአክሲዮኖቹ ራሳቸው የአክሲዮኖቹን ዋጋ ንግድ ሚኒስቴር በፈቀደው መሠረት በዝግ ሂሳብ እንዲሁም ኘሪሚየም ክፍያውን በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገባቸውን ደረሰኞች ቀጥታ ለመቅረዝ የጤና አገልገሎት አ.ማ. ማስረከብ አለባቸው፡፡ ማናቸውም ዳይሬክተር ወይም የድርጅቱ ሠራተኛ በምንም ዓይነት የአክሲዮን ሽያጭን ወይም ኘሪሚየምን ባለአክሲዮኑን ግለሰብ ወይም ድርጅት ወክሎ ገንዘብ መቀበል ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
- የተፈረመውን የአክሲዮን ሽያጭ ከጅምሩ በሙሉ ሆነ በከፊል ከሚከፍል ሰው በተፈረመው ሽያጭ መጠን ኘሪሚየሙ 5% በአንድ ጊዜ ተከፋይ ይሆናል፡፡
9. በአስገዳጅነት ሊከበሩ የሚገባቸው ደንቦች
የአክሲዮን ማኅበራት ካፒታል ማሳደግ አሠራር በሚመለከት የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ድንጋጌዎች የባለአክሲዮኖችንና የሌሎች ተደራሽ አካላትን መብትና ግዴታ ለማስከበር ሲባል በጥንቃቄ መከበር አለባቸው፡፡
10. በባንኮች ስለተከፈቱ የሂሳብ ዓይነቶች
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር ዝግ ሂሳብ (Blocked Account) እና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ (Current Account) በሚል ስያሜ የሚታወቁ ሁለት የሂሳብ ዓይነቶች በሀገር ውስጥ ባሉ ባንኮች ከፍቷል፡፡ የባንኮች የዝግና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ቁጥሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
የባንክ ሒሳብ መጠሪያ ስም፡ መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር
Account Name: MEQREZ HEALTH SERVICES SHARE COMPANY |
|||
ተ.ቁ | የባንኮች ስም | ዝግ ሒሳብ | ተንቀሳቃሽ ሒሳብ |
1 | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 1000342119488 | 1000342120109 |
2 | አባይ ባንክ | 1462113493011015 | 1461113493012012 |
3 | ሕብረት ባንክ | 1340411317961018 | 1341611317880018 |
4 | አቢሲኒያ ባንክ | 39635542 | 39921626 |
5 | አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ | 01322825718100 | 01303825718100 |
6 | ወጋገን ባንክ | 0840747530101 | 0840744510101 |
7 | ዳሸን ባንክ | 5059101578011 | 0059101576011 |
8 | ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ | 7000018309233 | 7000018309284 |
9 | ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ | 2759501001684 | 2759601000115 |
10.1. ዝግ ሂሳቦች (Blocked Account)
ከአክሲዮኖች ሽያጭ የሚሰበሰበው ገንዘብ የድርጅቱ ካፒታል ስለሆነ ይህም በዝግ ሂሳብ የሚቆየው የድርጀቱ የሥራ መጀመሪያ ካፒታል መጠን እስኪጠራቀም እና ድርጅቱ ሥራ ለመጀመር የንግድ ፈቃድ እስኪያገኝ ድረስ እንዲሁም በቦርዱ በዝግ ሂሳብ እንዲቆዩ ተጥሎ የነበረው እገዳ ሲነሳ ይሆናል፡፡
10.2. ተንቀሳቃሽ ሂሳብ (Current Account)
ከአክሲዮኑ ዋጋ በላይ ከባለአክሲዮኖች የሚሰበሰበው 5% (Premium) ገቢ የሚደረገው በተንቀሳቃሽ ሂሳብ የሚቀመጥ ሆኖ ሂሳቡን የሚያንቀሳቅሱት ገንዘቡ ለሥራ ማስኬጃ፣ ለኪራይ፣ ለቢሮ ዕቃዎችና መሣሪዎች መግዣ እንዲሁም ለደመወዝና ሌሎች አግባብነት ላላቸው ወጪዎች መውጣቱን የማረጋገጥ ኃላፊነት የዳይሬክተሮች ቦርድ ነው፡፡
ከዚህ ሂሳብ ወጪ ሆኖ የሚከፈል ገንዘብ በተቻለ መጠን አግባብ ባለው ደጋፊ ሰነዶች መታጀብ አለበት፡፡ የሂሳቡ እንቅስቃሴ በጠቅላላ ጉባኤው በተሰየሙ የሂሳብ ባለሙያዎች እየተመረመረ በመጨረሻ የተጠቃለለ የሂሳብ ሪፖርት ተዘጋጅቶ እንዲጸድቅ ለጠቅላላ የባለ አክሲዮኖች ጉባዔ ይቀርባል፤ በመጨረሻ ከተሰበሰበው ኘሪሚየም ከወጪ ቀሪ የሚተርፍ ካለ በተጨማሪ ካፒታል መልክ ለድርጅቱ ይሰጣል፡፡
11. የአክሲዮን ሽያጭ ለማሳለጥ የአክሲዮን ወኪሎች የመቅጠር አስፈላጊነት
የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክሲዮኖች ሽያጭ ለማሳለጥ የሚያግዙ ብቃት ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በኮሚሽን ክፍያ እና በጊዜያዊ የሥራ ውል መሰረት ቀጥሮ ማሰራት ይችላሉ፡፡
በአመዛኙ የአክሲዮኖችን ሽያጭ ለማፋጠን የዚህ ዓይነቱ አሠራር የሚካሄደው በራሳቸው ኮሚሽን ወኪሎች ብቻ ወይም አንዳንዴ እንደ አስፈላጊነቱ ከዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጋር በመተጋገዝ በጥምረት በመሥራት ነው፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ተግባር ድርጅቱ ከተሸጠው (ከተከፈለ) ሼር ካፒታል 3.5 % ኮሚሽን ሊከፍል ይችላል፡፡
በምንም ዓይነት የኮሚሽን ወኪሎች ገንዘብ ራሳቸው እንዲሰበስቡ (እንዲቀበሉ) አይፈቀድላቸውም፡፡ የአክሲዮን ሽያጩን በዝግ እና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ውስጥ ገቢ ማድረግ ያለበት ራሱ ባለአክሲዮኑ ወይም በእነሱ የሚወከለው ሰው ነው፡፡
12. ለአደራጆች የተፈቀዱ የተለዩ ጥቅማጥቅሞች
የአክሲዮን ኩባንያዎች የሚያቋቁሙ አደራጆች የ1952 ዓ.ም የንግድ ሕግ ሊከፈላቸው ስለሚቻል ጥቅማጥቅሞች ይደነግጋል፡፡ ይህም አደራጆች ሆነው በምሥረታው ባይሳተፉና ስማቸው በይፋ ባይመዘገብም ድርጅቱን ለማቋቋም ሃሳብ ያፈለቁትንም ያካትታል፡፡ የጥቅማጥቅሙን መጠን ለመወሰን የሚያስችለው ሥልጣን የተሰጠው ለአደራጆች ነው፡፡
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. አደራጆች ማለት አሁን የዳይሬክተሮች ቦርድ የሆኑት ለድርጅቱ እውን መሆን ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ከትርፍ ጋር በተያያዘ የሚከፈለው በንግድ ሕጉ እስከ 20 በመቶ ድረስ የተፈቀደው የትርፍ ክፍያ እንዳይከፈላቸው አደራጆች ተስማምተዋል፡፡
13. ለመሥራች ባለአክሲዮኖች የተፈቀዱ የተለዩ ጥቅማጥቅሞች
መሥራች ባለአክሲዮኖች የሚባሉት በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ ላይ የፈረሙ እና ማኅበሩን ያቋቋሙ እንዲሁም በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 307 ንዑስ አንቀጽ 4 ማኅበሩ እንዲፀና ሲሉ ማንኛውንም እርምጃ ለማኅበሩ ሥራ ያደረጉና ማኅበሩ የአክሲዮን ሽያጩን ባወጣበት በመጀመሪያው 3 ወራት እስከ ታኅሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ጊዜ ውስጥ ለገዙ ባለአክሲዮኖች በተከፈለው የአክሲዮን መጠን 10% ከተጣራ ትርፍ ላይ ተመድቦላቸዋል፡፡ ይህንንም ከትርፉ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዕኩል እንዲከፈላቸው ለጠቅላላ ጉባኤው የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
14. ሥለ ጤናው ዘርፍ ምልከታ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የሀገሪቱ የጤናው ዘርፍ ምልከታ (Outlook) አጠቃላይ መግለጫ እና የጤና ተቋማቱን ለማቋቋም አመክንዮ
በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው እ.ኤ.አ. የ2015 አጠቃላይ የዓለም ኢኮኖሚያዊ የሥራ አፈጻጸም በአማካይ የ3.1% ዓመታዊ እድገት፣ የአፍሪካ የ4.9% እና በተለይ ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ ንዑስ ቀጠና በአሁኑ ወቅት በተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታ ስለሚገኝ የ 8% እድገት ይኖረዋል የሚል ትንበያ ተመዝግቦበታል፡፡
ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች የጤናው ዘርፍ በባሕላዊ ሀኪሞች፣ በፋርማሲዎች እና የመድኃኒት ሱቆች ለትርፍ በተቋቋሙና ያለትርፍ አገልግሎት በሚሰጡ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች የሚከወን ተግባር ነው፡፡
ሰዎች የግሉን የጤና ዘርፍ የሚመርጡባቸው ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ከነዚህ ውስጥ ምቾት፣ ጥራት ያለው አገልግሎት አለ ብሎ ማመን እና የግል ሁኔታን ምሥጢራዊነት መጠበቅ ሲሆኑ ከሰሃራ በታች ይህ የሕክምና ሴክተር ለሀብታሞች ብቻ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው ለጤንነቱ ሲል የግሉን ዘርፍ ተመራጭ ያደርጋል (Africans of all socio-economic background turn to private sector for their health care needs.
የግሉ ዘርፍ መስፋፋት በመንግሥት ላይ ያለውን ሸክም ይቀንስል ፣ በጤና አጠባበቅ ፍላጎት እየጨመረ ይሄዳል ፣ ለሸማቾች ምርጫ እና ውድድር ይሰጣል ፡፡ የጤናው ዘርፍ ውጤታማነትን እና ጥራትን ለማሻሻል የሚረዳ ሲሆን ለጤና ፍትሃዊነትም አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የመክፈል አቅም ያላቸው ሰዎች የግል አገልግሎቶችን ለመጠቀም የሚከፍሉበት እና ሊከፍሉ የማይችሉት ደግሞ በተለያዩ አደረጃጀቶች ለመድረስ ያለመ ነው፡፡
የዓለም ባንክ አባል የሆነው ከዓለም አቀፉ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የወጣ አዲስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ጤና ላይ የሚውለው ወጪ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በእጥፍ እንደሚጨምር እና ከ 25 እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር ፍላጎቱን ለማሟላት እንደሚያስፈልግ እና የግል ዘርፍ ሚና ትልቅ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ የዚህ የምርምር ሪፖርት ዋና ግኝቶች-የግል የቴናው ዘርፍ የጤና አገልግሎትን በማቅረብ እና በገንዘብ ፋይናንስ ቀድሞውኑ ትልቅ ሚና የሚጫወተው ሲሆን በአማካይ 50 በመቶውን የኢንዱስትሪዎች እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ 60% የእነዚህ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ከዚሁ ሴክተር የሚመጡ ናቸው ፡፡ የአፍሪካ የጤና ወጭ በፍጥነት ማደጉን ይቀጥላል ፣ የግል ሴክተር እንዲሁ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በእጥፍ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በ 2005 እ.ኤ.አ በቢሊዮን የሚቆጠረው ወጪ በ2016 ወደ 35 ቢሊዮን ዶላር ገደማ በማደግ ፣ 60% ደግሞ ከግል ዘርፍ እንደሚመጣ ይጠበቃል፡፡ ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ የጤና አጠባበቅ ፍላጎቶችን ማሟላት ለጤና ሚኒስትሮች ትልቅ ፈታኝ ሥራ ነው ፡፡
ሀገራችን ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች አንዷ ስትሆን የጤና ችግር ያለባት እና በፍጥነት እያደገች ያለችም ነች፡፡ በድህነት ውስጥ ዝቅተኛ ትምህርት እና የጤና አገልግሎቶች ውስንነት ለጤንነት ችግሮች ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው ፡፡ በተጨማሪም የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱ ደካማ ሲሆን ሽፋኑም በጥሩ ሁኔታ የተደራጀ አይደለም ፡፡ በኢትዮጵያ የግል የጤና አገልግሎት መስጫ ሀብቶችን ማሰባሰብ እና በጤና ስርዓት ውስጥ ቅልጥፍናን ለማሻሻል ከሚያስገድዱ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በህጋዊም ሆነ ከህግ ውጪ በሥራ ፣ በንግድ ወይም በትምህርት ምክንያት በገጠር አካባቢዎች ፈጣን የከተማ ልማት እና የከተማ ፍልሰት በፍጥነት እያደገ መምጣቱ ነው ፡፡ የግለሰቦችን ጤናማ መሆን በተለይም በከተሞች ውስጥ እድገትን የሚያበረታቱ ምክንያቶች ናቸው ፡፡
ድምዳሜ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ የጤናው ዘርፉ ሊሰጠው ከሚገባው ትኩረትና ለተሻለ ሕክምና የፍላጎት ከፍተኛነት፣ እ.ኤ.አ. በ2040 የኢትዮጵያ ሕዝብ 180 ሚሊዮን በላይ ይደርሳል የሚል ትንበያ የሚፈጥረው ከፍተኛ የአገልግሎት ፍላጐት፣ እስካሁን በአካሄድነው አጠቃላይ የአዋጭነት ጥናት መሰረት መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. መመስረት ማኅበረሰባዊ ተፈላጊነት ያለው (Economically desirable) ፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የጐላና (Economically feasible) በፋይናንስ አንጻር ደግሞ ትርፋማ (Financially profitable) እንደሚሆን በእርግጠኝነት ያመላክታል፡፡
ፍቅር እና አክብሮት የተሞላበት የላቀ እንክብካቤ