ማስታወቂያ
የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 393 እና 394 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9 መሠረት የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ጀምሮ ካሳንችስ ወሳኝ ኩነት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘውና ቀድሞ ዮርዳኖስ ሆቴል የነበረው የአክሲዮን ማኅበሩ አዲስ የጠቅላላ ሆስፒታል ሕንፃ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ…
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ.
በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻ ገበያ ሥርዓት ተጠቅመው በጤናው ዘርፍ ላይ በማተኮር በጤናው የአገልግሎት ዘርፍ እንዲሁም የገቢና ወጭ ንግድ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሁሉ የተሻለ አማራጭ በመሆንና አገልግሎት በማቅረብ ለሀገሪቱ አጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ተገቢ ድርሻ ለማበርከት አስበውና ራዕይ ሰንቀው በተነሱ የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በሆኑት የቀድሞው አደራጆች በወጠኑት ዓላማ የተስማማሙ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በወሰኑ 102 በሚሆኑ በጤናው ዘርፍ ረጅም ልምድ እና ክህሎት ባዳበሩ እና በአስተዳደር፣በፋይናንስ እና በተቋም አመራር የላቀ ልምድ ባላቸው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በ 1952 ዓ.ም በወጣው የንግድ ሕግ መሠረት በተከፈለ ካፒታል ብር 4 170 000.00 በመስከረም 12 2013 ዓ.ም በምዝገባ ቁጥር ፡ AR/AA/3/0006864/2013 መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ተቋቋመ፡፡
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎቱን ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ
/in News /by Tewodrosመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ
/in News /by Tewodrosየመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ሐምሌ 1 2013 ዓ.ም አራዘመ
/in News /by etechየመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ሚያዚያ 13 2013 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ሐምሌ 1 2013 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ገለጸ፡፡
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ መጋቢት 30 2013 ዓ.ም አራዘመ
/in News /by tcየመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ በ የካቲት 1 2013 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ መጋቢት 30 2013 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ገለጸ፡፡
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ጥር 30 2013 ዓ.ም ብቻ አራዘመ
/in News /by tcእንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ በ ታኅሳስ 28 2013 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ጥር 30 2013 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ገለጸ፡፡