ማስታወቂያ
የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 393 እና 394 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9 መሠረት የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ጀምሮ ካሳንችስ ወሳኝ ኩነት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘውና ቀድሞ ዮርዳኖስ ሆቴል የነበረው የአክሲዮን ማኅበሩ አዲስ የጠቅላላ ሆስፒታል ሕንፃ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ…
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ.
በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻ ገበያ ሥርዓት ተጠቅመው በጤናው ዘርፍ ላይ በማተኮር በጤናው የአገልግሎት ዘርፍ እንዲሁም የገቢና ወጭ ንግድ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሁሉ የተሻለ አማራጭ በመሆንና አገልግሎት በማቅረብ ለሀገሪቱ አጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ተገቢ ድርሻ ለማበርከት አስበውና ራዕይ ሰንቀው በተነሱ የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በሆኑት የቀድሞው አደራጆች በወጠኑት ዓላማ የተስማማሙ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በወሰኑ 102 በሚሆኑ በጤናው ዘርፍ ረጅም ልምድ እና ክህሎት ባዳበሩ እና በአስተዳደር፣በፋይናንስ እና በተቋም አመራር የላቀ ልምድ ባላቸው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በ 1952 ዓ.ም በወጣው የንግድ ሕግ መሠረት በተከፈለ ካፒታል ብር 4 170 000.00 በመስከረም 12 2013 ዓ.ም በምዝገባ ቁጥር ፡ AR/AA/3/0006864/2013 መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ተቋቋመ፡፡
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ሽያጩን ለማፋጠን የአክሲዮን ሻጭ ኤጀንት ሊጠቀም መሆኑ ተገለጸ
/in News /by tcየቦርዱ ም/ሰብሳቢ እና የማርኬቲንግ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተስፋየ ቢሆነኝ ዛሬ ጥቅምት 9 2013 ዓ.ም እንደተናገሩት ያቀድናቸውን እቅዶች በቶሎ ወደ ሥራ ለማስገባት የአክዮን ሻጭ ኤጀንት መጠቀሙ አስፈላጊ መሆኑን ተናገሩ፡፡
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በቅርቡ ለቴርሺያሪ ሆስፒታል ግንባታ የሚሆነውን ቦታ ከመንግስት በሊዝ ሊጠይቅ መሆኑ ተሰማ
/in News /by tcመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በቅርቡ ለቴርሺያሪ ሆስፒታል ግንባታ የሚሆነውን ቦታ ከመንግስት በሊዝ ሊጠይቅ መሆኑ በጥቅምት 8 2013 ዓ.ም. ቦርዱ ባደረገው ስብሰባ ላይ መወሰኑን የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ማኅተመ በቀለ ተናገሩ፡፡
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር ካፒታል ለማሳደግ ውሳኔ አሳለፈ
/in News /by tcመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በጥቅም 1 2013 ዓ.ም ባካሄደው ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የድርጅቱን ካፒታል በብር 518 ሚሊዮን ለማሳደግ ወሰነ፡፡
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር አንደኛ መደበኛ እና አንደኛ ድንገተኛ ጉባኤው በደማቅ ሁኔታ አካሄደ
/in News /by tcመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር እሁድ ጥቅምት 1 2013 ዓ.ም. አንደኛ መደበኛ እና አንደኛ ድንገተኛ ጉባኤውን በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል አካሄዷል፡፡ በጉባኤውም ላይ ሼር ከገዙ ባለአክሲዮኖች 72 በመቶው በራሳቸው እና በተወካያቸው ተገኝተዋል፡፡