መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎቱን ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በጤናው ዘርፍ ያለውን ሰፊ የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት የተቋቋመ እንደመሆኑ ባስቀመጠው ፍኖተ ካርታ መሠረት የመጀመሪያ የሆነውን የጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ፡፡

ለሆስፒታል አገልግሎት የሚሆን ሕንጻም ካዛንቺስ አካባቢ መከራየቱንና ለሱም የሚያስፈልጉ ሥራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን ከአራት እስከ ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገልጻል፡፡
ሆስፒታሉ አገልግሎቱን ሲጀምር በዋናነት ተገልጋዮች የሚረኩበት ጥራቱ ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት መስጠት፣ በሀገራችን በግሉ ዘርፍ የማይሰጡ የጤና አገልግሎቶችን መጀመር እንዲሁም ወደ ውጪ የሚሄደውን ታካሚ በሀገር ውስጥ የተሻለ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ ላይ እንደሚሠራ ተነግራል፡፡

በተያያዘ ዜናም መቅረዝ የኢሜጂንግ ዲያግኖስቲክ ማእከሉን ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን ማጠናቀቁ ተገልጻዋል፡፡ የመድኃኒት እና ሕክምና መሳሪያዎች እንዲሁም የማማከር እና ምርምር ዘርፎችም ላይ አስፈላጊ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በቀጣይ በጀት ዓመት ለመጀመር ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ተብሏል፡፡