ለመቅረዝ ቤተሰቦች!

እንኳን ደስ አላችሁ!

መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የጊዜ ገደብ እንዲራዘም ወስኗል። በዚሁ መሠረትም፤

፩. እስከ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አክሲዮን የገዛችሁ ነባር መሥራች ባለአክስዮኖች
ይህንን ታላቅ ርዕይ ያለው ትርፈማ ተቋም መስራች ስለሆኑ እንኳን ደስ አለዎት እያልን ቀሪ ክፍያ ያለብዎ ከሆነ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት እንዲያጠናቅቁ እና ከፍለው የጨረሱ ከሆነ አክስዮን በማሳደግ ተቋምዎ ወደ አገልግሎት በፍጥነት እንዲገባ በማድረግ የበለጠ ትርፋማ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት እያሳሰብን አክስዮን በሚያሳድጉበት ወቅት የ5% የአገልግሎት ክፍያ የማይጠየቁ መሆኑን በዚሁ ማስታወስ እንወዳለን።

፪. አዳዲስ ለሚገቡ ባለአክስዮኖች
የሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤን ተከትሎ የዳይሬክቶች ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ከመጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ አነስተኛ መግዛት የሚቻለው የአክስዮን መጠን ብር 40 ሺህ ሆኖ የአከፋፈል ሁኔታውም በአንድ ጊዜ ሙሉ መሆኑን እና የአገልግሎት ክፍያ 5 በመቶ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

፫. የመስራችነት ጊዜም እስከ ሚያዚያ 30 2014 ዓ.ም ብቻ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን በመጨረሻ ሠዓት ከሚከሰት አላስፈላጊ ሩጫ አሁኑኑ አክስዮኑን በመግዛት የአክስዮን ድርጅቱ ባለቤት እንዲሆኑ ስንገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው።