የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ሐምሌ 1 2013 ዓ.ም አራዘመ

የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ሚያዚያ 13 2013 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የመሥራችነት ጥቅም የሚያስገኘውን የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ሐምሌ 1 2013 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ገለጸ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ማኅተመ በቀለ ሲናገሩ በተደጋጋሚ አክሲዮኑን ለመግዛት ባሰቡ ሰዎች ከተለያዩ የዓለማችን ክፍል ባሉ ወንድሞች እና እህቶች ለመግዛት ጊዜው እንዳጠረባቸው ባሉን የመገናኛ መንገዶች በሙሉ በተደጋጋሚ ጠይቀውናል፡፡ ለዚህም መልስ መስጠት በጣም አስፈላጊ መሆኑንና እንዲሁም የመቅረዝን ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው በማሰብ መራዘሙን ገልጸዋል፡፡

አፈጻጸሙን በተመለከተ ሲናገሩ ለመጀመሪያው አንድ ወር ( ከሚያዚያ 15 2013 እስከ ግንቦት 15 2013) ከ 40 ሺህ ብር ጀምሮ አክሲዮን የሚገዙ በሙሉ መሥራች መሆን እንደሚችል፤ ከ ግንቦት 16 2013 እስከ ሰኔ 15 2013 ደግሞ ብር 50ሺህ እንደሚሆን ከሰኔ 16 2013 እስከ ሐምሌ 1 2013 ደግሞ 60ሺህ ብር እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ ይኸ ማለት በ ሃያ ሺህ ብር መግዛት ይከለከላል ሳይሆን የመሥራችነት ጥቅም ግን አያገኙም ማለት ነው፡፡ስለዚህ ብዙኀኑ እንዲሳተፍ የተራዘመውን የአክሲዮን ሽያጭ በአግባቡ እንጠቀምበት፤ ሌሎች አላማውን አውቀው እንዲሳተፉ እንድንቀሰቅስ የሚል መልእክትን አስተላልፈዋል፡፡