የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 393 እና 394 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9 መሠረት የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ የካቲት 27 ቀን 2014 .ከቀኑ 730 ሰዓት ጀምሮ ካሳንችስ ወሳኝ ኩነት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘውና ቀድሞ ዮርዳኖስ ሆቴል የነበረው የአክሲዮን ማኅበሩ አዲስ የጠቅላላ ሆስፒታል ሕንፃ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

2ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየምና ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
  2. 2ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች ማጽደቅ
  3. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል
  4. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2013 .. በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2014 በጀት ዓመትን የትኩረት አቅጣጫዎችን መስማት እና ማጽደቅ
  5. የውጭ ኦዲተርን ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
  6. በተጓደሉ የቦርድ አባላት ምትክ የቦርድ አባላት ሹመት ማጽደቅ
  7. የዲሬክተሮች ቦርድ አክሲዮናቸውን ያሳደጉ ነባር፣ አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖች በመወከል በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በመቅረብ እንዲፈርሙ ውክልና ስለመስጠት፣
  8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን አበል ማጽደቅ
  9. አዲስ የሚገቡ ባለአክሲዮኖችን በመሥራች አባልነት እንዲመዘገቡ የሚቀበልበትን ጊዜ መወሰን
  10. 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለጉባኤን ማጽደቅ

ማሳሰቢያ

  • በጉባኤው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ /ማስክ/ ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባኤው ከመካሔዱ በፊት አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ1ኛ ፎቅ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ቢሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ ሲሆን ተወካዮቻችሁ በሰነዶች ማረጋገጫ መ/ቤት የተረጋገጠ የውክልና ፎርሙን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን +251991737373 /+251973830673 ማግኘት ይቻላል፡፡

የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ..